እውን ሆኗል
ኢቲኬር የጤና እና ውበት መጠበቂያ ምርቶች ሽያጭ በስፓይሩሊና ምርት ተጠቃሚነት ላይ የአርክቦት የስምምነት ፊርማውን አከናወነ።
በዛሬው እለት በጌትፋም ሆቴል በተከናወነው የፊርማ ስነስርአት ላይ የኢቲኬር መስራችና ባለቤት አቶ ማቴዎስ መባ፣ የኢቲኬር ስፓይሩሊና መሪ ተመራማሪ ዶ/ር ሀብቴ ጀቤሳ፣ የኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት ብርሃኑን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የስምምነት ፊርማውንም በኢቲኬር በኩል የድርጅታችን መስራችና ባለቤት አቶ ማቴዎስ መባ በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት በኩል ዶ/ር አብዮት ብርሀኑ ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የድርጅታችን መስራችና ባለቤት አቶ ማቴዎስ መባ ይህን ስምምነት የማህበረሰብ ተጠቃሚነት እና የብዝሀ ህይወት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንፃር በርካታ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዮት ብርሀኑ በበኩላቸው ኢቲኬር ይህንን ተነሳሽነት ወስዶ ይህንን ፕሮጀክት መጀመሩ እንደ ሀገር የብዘሀ ህይወት ሀብቶችን በማሳወቅ እና በመጠቀም ረገድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል።
በዚህ መሰናዶ ላይ የኢቲኬር የቺፍ ሰርክል አባላት፣ የሊድቲም አባላት፣ ታላላቅ መሪዎች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የሚዲያ አካላት እንዲሁም የ ኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
