ከአዲስ አበባ በ 720 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ኢቲኬር የሚል ስም በደማቁ ተፅፏል። ዛሬ ማለዳ የኢቲኬር መስራች እና ባለቤትን ጨምሮ በርካታ የማኔጅመንት እና የኢቲኬር መሪዎችን የያዘ ቡድን ለአንድ ታላቅ አላማ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ሀዋሳ አርባምንጭ ጂንካን አልፎ አሪ ዞን ከሀገሬው ወንዝ ከዋልሸት ማዶ ተገኝቷል። ላለፉት ወራት ሲደረጉ ከነበሩ በርካታ ውይይቶች እና ፍሬያማ ንግግሮች በኋላ ኢቲኬር የውበት መጠበቂያ ምርቶች ሽያጭ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ እስካሁን ከተለያዩ ቦታዎች ሲሰበሰቡ የነበሩ የምርቶቻችን ጥሬ እቃነት የሚያገለግሉ የኸርባል ምርቶችን ለማብቀል ምቹ የሆነ የግብርና መሬት በኢንቨትመንት ለማልማት ተረክቧል።
እንደ ቀዳሚዎቹ የአለማችን ቀጥተኛ ሽያጭ ኢንዱስትሪዎች ሁሉ አሎቬራን ጨምሮ በርካታ ምርቶችን በራስ አቅም በማፍራት ከእርሻ እስከ የውበት እና ጤና መጠበቂያ ምርትነት የሚደረገውን ጉዞ እውን ያደረገውን ይህንን የግብርና ቦታ በዛሬው እለት የድርጅታችን መስራችና ባለቤት አቶ ማቴዎስ መባ መሪነት ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የኢቲኬር ኤሊት አምባሳደር ተመስገን ሀይሉን ጨምሮ ታላላቅ ሊደሮች በዞኑ በመገኘት 300 ሄክታር የእርሻ ቦታ ርክክብ ተደርጓል።
በርክክብ ስነስርአቱ ላይ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የኢንቨስትመንት ቢሮ ተወካዮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
ኢቲኬር ይህንን የእርሻ መሬት በማልማት በሀገራችን ቀዳሚው የቀጥተኛ ሽያጭ ኩባንያ የሚያደርገው ሲሆን ይህ ስፍራ ወደ ምርት ሲገባ ሬትን ጨምሮ ኢቲኬር የሚጠቀምባቸውን ተፈጥሯዊ እፅዋት ከማምረት ባለፈ በርካታ አዲስ ግብአቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሪን ለማዳን አይነተኛ ሚና የሚጫወት ስፍራ እንደሚሆን ይጠበቃል።
